የህጻናት ያለእድሜ ጋብቻ ተከላካይ አርበኚት የትግል ጥሪ
-
0:01 - 0:03ዛሬ ንግግሬን
-
0:03 - 0:05ግጥም በማንበብ እጀምራለሁ
-
0:05 - 0:08ማላዊ ከምትገኝ ጓደኛዬ የተጻፈ ነው
-
0:08 - 0:10አይሊን ፒይሪ ትባላለች
-
0:10 - 0:14አይሊን ፒይሪ የ13 አመት ልጅ ነች
-
0:14 - 0:19ጽፈናቸው ከነበር የግጥም
ስብስቦች መካከል ስፈልግ -
0:19 - 0:22የሷን አስደናቂ ግጥም አገኘሁ
-
0:22 - 0:24በጣም ያነሳሳል!
-
0:24 - 0:26ስለዚህ እሱን አነብላቹሀለው
-
0:27 - 0:31ለግጥሙ የሰጠችው አርዕስ
"ስፈልግ ነው የማገባው" ይላል -
0:31 - 0:33(ሳቅ)
-
0:33 - 0:36ስፈልግ ነው የማገባው!
-
0:36 - 0:41እናቴ ልታስገድደኝ
አትችልም እንዳገባ -
0:41 - 0:44አባቴ ሊያስገድደኝ
አይችልም እንዳገባ -
0:46 - 0:48አጎት ፣ አክስቶቼ
-
0:48 - 0:51ወንድም ፣ እህቶቼ
-
0:51 - 0:53ሊያስገድዱኝ አይችሉም እንዳገባ
-
0:54 - 0:56ማንም በዚች አለም
-
0:56 - 1:00አይችልም ተገድጄ እንዳገባ
-
1:00 - 1:02ስፈልግ ነው የማገባው!
-
1:02 - 1:05ብትደበድቡኝም
-
1:05 - 1:08ብታባሩኝ እንኳን
-
1:08 - 1:11ምንም ብታደርጉ መጥፎ
-
1:11 - 1:17ስፈልግ ነው የማገባው!
-
1:17 - 1:21ሳልጨርስ አይደለም
ሳልማር ትምህርቴን -
1:21 - 1:25ሳይደረስ አይደለም
ሳላድግ በእድሜ -
1:25 - 1:28ስፈልግ ነው የማገባው!
-
1:29 - 1:32ይህ ግጥም ግር ሊላቹ ይችላል
-
1:32 - 1:35በ13 አመት ልጅ መጻፉ
-
1:35 - 1:40ግን እኔና አይሊን
ከመጣንበት አካባቢ -
1:40 - 1:44ይሄ ግጥም
-
1:44 - 1:48የአርበኞች ጥሪ ነው!
-
1:48 - 1:51እኔ ከማላዊ ነው የመጣሁት
-
1:51 - 1:55ማላዊ ደሀ ከሚባሉ አገራት አንዷነች
-
1:55 - 1:58በጣም ደሀ!
-
1:58 - 2:03የጾታ እኩልነት አጠራጣሪ የሆነባት አገር
-
2:03 - 2:05በዛች አገር በማደጌ
-
2:05 - 2:08በህይወቴ ውስጥ የራሴን ምርጫ
ማድረግ አልችልም -
2:08 - 2:10በህይወት የማንነት እድሎችን
እንኳን... -
2:10 - 2:13መመርመር አልችልም
-
2:13 - 2:16አንድ ታሪክ ልንገራችሁ
-
2:16 - 2:18ስለ ሁለት የተለያዩ ልጃገረዶች ነው
-
2:18 - 2:22ስለ ሁለት ውብ ልጃገረዶች
-
2:22 - 2:25እነዚህ ልጆች
-
2:25 - 2:27በአንድ ጣራ ስር አብረው ነው ያደጉት
-
2:27 - 2:29አንድ አይነት ምግብ እየበሉ
-
2:29 - 2:32አንዳንዴ አንድ ልብስ እየተጋሩ
-
2:32 - 2:35ጫማ አንኳን ሳይቀር
-
2:35 - 2:40ግን የህይወት ጉዟቸው የተለያየ ሆነ
-
2:40 - 2:42በሁለት የተለያዩ መንገዶች
-
2:43 - 2:47ሁለተኛዋ ልጅ ታናሽ እህቴ ናት
-
2:47 - 2:52ታናሽ እህቴ 11 አመት ይሆናት ነበር
-
2:52 - 2:54ባረገዘችበት ወቅት
-
2:56 - 3:00በጣም የሚያሳምም ነገር ነው!
-
3:01 - 3:05እሷ ብቻ አይደለችም
እኔም ተጎድቻለሁ -
3:05 - 3:08የጭንቅ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩት
-
3:08 - 3:12በባህላችን
-
3:12 - 3:15ለአቅመ ሄዋን በደረስን ጊዜ
-
3:15 - 3:19ወደ ልምምድ ካምፕ
መሄድ ይኖርብናል -
3:19 - 3:21በነዚህ ካምፖች
-
3:21 - 3:25ወንድን በጻታ ግንኙነት
እንደምታስደስቱ ትማራላቹ -
3:25 - 3:27ልዩ የሆነ ቀን አለ
-
3:27 - 3:30"በጣም ልዩ ቀን"
ብለው የሚጠሩት -
3:30 - 3:33በማህበረሰቡ የተቀጠረ ወንድ
-
3:33 - 3:35ወደ ካምፑ ይመጣና
-
3:35 - 3:38ከሴት ህጻናቱ ጋር እንዲተኛ ይደረጋል
-
3:39 - 3:42አስቡት እስቲ!
እነዚህ ሴት ህጻናት ያለባቸውን ስቃይ -
3:42 - 3:45በየቀኑ!
-
3:47 - 3:50አብዛኞቹ ልጃገረዶች ያረግዛሉ!
-
3:50 - 3:53በኤችአይቪ ኤድስ ይያዛሉ!
-
3:53 - 3:55ሌሎች በጾታ ግንኙነት
የሚመጡ በሽታዎች ጭምር -
3:56 - 4:01ትንሷ እህቴ እርግዝና ነበር የገጠማት
-
4:01 - 4:05አሁን 16 አመቷ ነው
-
4:05 - 4:08ሶስት ልጆች አሉዋት
-
4:08 - 4:11የመጀመሪያ ትዳሯ አልሰመረም
-
4:11 - 4:15ሁለተኛውም ቢሆን እንደዛው
-
4:15 - 4:19በሌላ በኩል ደግሞ ይህቺ ልጅ አለች
-
4:19 - 4:21የምታስደንቅ ናት!
-
4:21 - 4:23(ሳቅ)
-
4:23 - 4:26(ጭብጨባ)
-
4:28 - 4:30አስደናቂ ነች ያልኩት ስለሆነች ነው!
-
4:30 - 4:33በጣም አስደማሚ ናት!
-
4:33 - 4:37ያቺ ልጅ እኔ ነኝ! (ሳቅ)
-
4:37 - 4:40የ13 አመት ልጅ ሆኜ
-
4:40 - 4:43አድገሻል
-
4:43 - 4:46እድሜሽ ደርሷል
-
4:46 - 4:50ወደ ልምምድ ካምፑ
መሄድ አለብሽ ሲሉኝ ነበር -
4:50 - 4:53"ምን?" ነበር የኔ መልስ
-
4:53 - 4:57ወደ ልምምድ ካምፑ አልሄድም አልኩ
-
4:58 - 5:01አንድ ሴት ምን እንዳለችኝ ታውቃላቹ?
-
5:01 - 5:05ደደብ ልጅ ነሽ!
ምንም የማይገባሽ! -
5:05 - 5:12የማህበረሰባችንን፣
የእኛን ባህል አታከብሪም! -
5:12 - 5:16እንቢ! ያልኩት
የት እንደምሄድ ስለማውቅ ነው -
5:16 - 5:18በህይወቴ ምን አንደምፈልግ
ስለማውቅ ነው -
5:20 - 5:23በልጅነት ብዙ ህልሞች ነበሩኝ
-
5:24 - 5:28በደንብ መማር እፈልግ ነበር
-
5:28 - 5:30ወደፊት ጥሩ ስራ አንዲኖረኝ
-
5:30 - 5:32እራሴን ጠበቃ ሆኜ እስለው ነበር
-
5:32 - 5:35ትልቅ ወንበር ላይ ተቀምጬ
-
5:35 - 5:37በሀሳብ የምስለው
-
5:37 - 5:40በየቀኑ በአእምሮዬ የሚመላለሰው
እሱ ነበር -
5:40 - 5:42ደግሞ አውቅ ነበር
አንድ ቀን -
5:42 - 5:47የሆነ ነገር፣ የሆነ ትንሽ ነገር ለ
ማህበረሰቤ እንደማበረክት -
5:47 - 5:49ግን እንቢ ካልኩኝ በኋላ በየቀኑ
-
5:49 - 5:51ሴቶቹ
-
5:51 - 5:55"እራስሽን ተመልከቺ እስቲ? ትልቅ ሆነሻል!
እህትሽ አንኳን ልጅ አላት! -
5:55 - 5:56አንቺስ?" ይሉኛል
-
5:56 - 6:01ይሄን ዘፈን ነበር
በየቀኑ እሰማ የነበረው -
6:01 - 6:05ይሄን ዘፈን ነበር
በየቀኑ ልጆቹ ይሰሙ የነበረው -
6:05 - 6:09ምንም ሳያደርጉ ሲቀሩ ማህበረሰቡ እንዲሆኑ የሚፈልገው እሱን ነው
-
6:12 - 6:15የኔንና የእህቴን ታሪክ ሳነጻጽረው
-
6:15 - 6:20ለራሴ "የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ?" አልኩ
-
6:20 - 6:25አንድ ነገር መለወጥ
ለምንድ ነው የማልችለው? -
6:25 - 6:28ያውም! ከጥንት ጀምሮ የነበረን ነገር
-
6:28 - 6:30በዛን ጊዜ ነው
ሌሎቹን ልጆች የሰበሰብኳቸው -
6:30 - 6:33ልክ እንደ እህቴ ልጆች ያላቸውን
-
6:33 - 6:36ይማሩ ነበር ግን ማንበብና መጻፍ
ጠፍቶባቸዋል -
6:36 - 6:38ኑና እርስ በራሳችን እንማማር
አልኳቸው -
6:38 - 6:40ማንበብና መጻፍ እንደገና እንሞክር
-
6:40 - 6:44ብእር እንዴት እንደሚያዝ፣
እንዴት እንደሚነበብ፣
መጽሀፍ እንደሚያዝ -
6:44 - 6:48በጣም ትልቅ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው
-
6:48 - 6:52ስለ እነርሱ ትንሽ አወኩኝ
-
6:52 - 6:56የግል ታሪካቸውን ያጫውቱኝ ነበር
-
6:56 - 6:57በእናትነታቸው
-
6:57 - 7:00በየቀኑ ስለሚገጥማቸው ነገር
-
7:00 - 7:02ያኔ ሀሳብ መጣልኝ
-
7:02 - 7:06እነዚህ በኛ ላይ የሚሆኑትን
ነገሮች ይዘን -
7:06 - 7:10ለእናቶቻችን ለባህላዊ መሪዎቻችን
ለምን አንነግራቸውም? -
7:10 - 7:12እነዚህ ነገሮች ስህተት አንደሆኑ
ለምን አናስረዳም? -
7:12 - 7:14ለማድረግ የሚያስፈራ ነገር ነበር
-
7:14 - 7:16ምክንያቱም ባህላዊ መሪዎቻችን
-
7:16 - 7:18አምነው የተቀበሉት ልማድ ነው
-
7:18 - 7:21ለዘመናት የነበረ ነገር ነው
-
7:21 - 7:22ለመቀየር የሚከብድ ነገር
-
7:22 - 7:25ግን ለመሞከር ጥሩ የሆነ
-
7:25 - 7:27ስለዚህ ሞከርነው!
-
7:27 - 7:30በጣም ከባድ ነበር ግን ገፋንበት
-
7:30 - 7:33እናም አሁን በማህበረሰባችን
-
7:33 - 7:36የመጀመሪያዎቹ ሴቶች ነን
-
7:36 - 7:39መሪዎቻችንን ስንጫን
-
7:39 - 7:43እናም መሪዎቻችን ከጎናችን ቆሙው
-
7:43 - 7:46ማንም ሴት 18 አመት ሳይሞላት
ማግባት የለባትም አሉ -
7:46 - 7:50(ጭብጨባ)
-
7:54 - 7:55በማህበረሰባችን
-
7:55 - 7:58ለመጀመሪያ ጊዜ
-
7:58 - 8:00በህግ ደረጃ
-
8:00 - 8:04የመጀመሪያው
ሴት ልጆችን የሚከላከል ህግ -
8:04 - 8:06ሆነ!
-
8:06 - 8:08እዚህ ጋር አላቆምንም
-
8:08 - 8:11ወደፊት ተራመድን
-
8:11 - 8:15በኛ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን
ለያንዳንዷ ሴት ህጻን መብት ለመዋጋት ቆረጥን -
8:15 - 8:17በሌላም ማህበረሰብ ቢሆን
-
8:17 - 8:22የህጻናት የጋብቻ ህግ በቀረበበት ጊዜ
-
8:22 - 8:25በአገሪቱ ፓርላማ ተገኝተን ነበር
-
8:25 - 8:29በየቀኑ የፓርላማ አባላቱ
በሚገቡበት ሰአት -
8:29 - 8:32እባካችሁ ህጉን ደግፉ!
እንላቸው ነበር -
8:32 - 8:37እዚህ አንዳለው አይነት
ቴክኖሎጂ አልነበረንም -
8:37 - 8:39ግን ትናንሽ ስልኮች ነበሩን
-
8:39 - 8:44ስለዚህ ቁጥራቸውን ፈልገን
ለምን በጽሁፍ መልክት አንልክላቸውም? ተባባልን -
8:44 - 8:47አደረግነው! ጥሩ ነገር ነበር!
-
8:47 - 8:49(ጭብጨባ)
-
8:49 - 8:52ህጉ ከጸደቀ በኋላ
መልሰን በጽሁፍ መልክት ላክንላቸው -
8:52 - 8:55"ህጉን ስለደገፋቹ እናመሰግናለን"
-
8:55 - 8:56(ሳቅ)
-
8:56 - 8:59ፕሬዝዳንቱ ህጉን
በፊርማው ሲያጸድቅ -
8:59 - 9:03ቋሚ ሆነ!
ይሄ ተጨማሪ ድል ነበር -
9:03 - 9:08አሁን በማላዊ የጋብቻ እድሜ 18 አመት ነው
ከ15 እስከ 18 -
9:08 - 9:12(ጭብጨባ)
-
9:14 - 9:18የህጉ መጽደቅ በራሱ ጥሩ ነገር ነበር
-
9:18 - 9:21ግን አንድ ነገር ልንገራቹ
-
9:21 - 9:2618 አመት የጋብቻ እድሜ
የሆነባቸው አገሮች አሉ -
9:26 - 9:30ግን በየቀኑ የሴቶች የህጻናት ለቅሶ
እየሰማን አይደለም? -
9:30 - 9:35በየቀኑ የሴት ህጻናቱ
ህይወት ይባክናል -
9:35 - 9:42ከመሪዎቻችን አሁን የሚያስፈልገው
የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ነው -
9:42 - 9:44ቃል ማክበር ማለት
-
9:44 - 9:50የሴት ህጻናትን ጉዳይ
ሁሌም ከልብ መያዝ ነው -
9:50 - 9:54እንደ ሁለተኛ ደረጃ መታየት የለብንም
-
9:54 - 9:58ማወቅ ያለባቸው ነገር!
ሴቶች በዚህ ክፍል ውስጥ እንዳለነው -
9:58 - 10:01ሴት ብቻ! ልጆች ብቻ!
አይደለንም! -
10:01 - 10:03ከምንም ነገር በላይ ነን!
-
10:03 - 10:05የተሻለ ማድረግ እንችላለን
-
10:05 - 10:08ስለ ማላዊ ሌላው ነገር
-
10:08 - 10:11በማላዊ ብቻ አይደለም
በሌሎችም አገሮች -
10:11 - 10:15ያሉት ህጎች
-
10:15 - 10:20ህግ እስካልተፈጸመ ድረስ
ህግ አይሆንም -
10:20 - 10:24በቅርብ ያጸደቅነው ህግ
-
10:24 - 10:26በሌሎች አገራትም ያለው ህግ
-
10:26 - 10:30በየአካባቢው መሰራጨት አለበት
-
10:30 - 10:33በየማህበረሰቡ
-
10:33 - 10:38የሴት ህጻናት ጉዳይ
አስቸጋሪ በሆነበት ሁሉ -
10:38 - 10:43በየቀኑ በማህበረሰብ ደረጃ
ሴት ህጻናት ከባድ ችግር ይጋረጥባቸዋል -
10:43 - 10:48ስለዚህ እነዚህ ሴት ህጻነት
የሚጠብቃቸው ህግ አንዳለ ካወቁ -
10:48 - 10:51ተነስተው እራሳቸውን መከላከል
ይችላሉ -
10:51 - 10:55ምክንቱም የሚጠብቃቸው ህግ
እንዳለ ስለሚያውቁ ነው -
10:57 - 11:01ሌላ ማለት የምፈልገው
-
11:01 - 11:06የሴት ህጻናት፣ የሴቶች የትግል ድምጽ
-
11:06 - 11:09ውብ ነው! ሁሉም ጋር አለ
-
11:09 - 11:12ይሄንን ግን ብቻችንን
ማድረግ አንችልም -
11:12 - 11:15ወንዶች ትግላችንን ሊቀላቀሉን
-
11:15 - 11:17ከጎን ሆነው አብረን መስራት አለብን
-
11:17 - 11:19የጋራ ሀላፊነት ነው!
-
11:19 - 11:22ለሴት ህጻናት የሚያስፈልገውን ሁሉ መሟላት አለበት
-
11:22 - 11:28ጥሩ ትምህርት፣ ከሁሉም በላይ
በ11 አመት አለመዳር -
11:30 - 11:33በተጨማሪ
-
11:33 - 11:36አንድ ላይ ከሆንን
-
11:36 - 11:40ህግን
-
11:40 - 11:43ባህላዊና ፖለቲካዊ ዳራን
-
11:43 - 11:48የሴት ህጻናትን መብት የሚነፍገውን
መቀየር እንችላለን -
11:48 - 11:53እዚህ ከፊታቹ በመሆን ዛሬ
-
11:53 - 12:00ለትውልዶች ያለ እድሜ ጋብቻን
ማስቆም እንደምንችል እነግራቹሀለው -
12:01 - 12:03በዚች ቅጽበት!
-
12:03 - 12:07ሴት ህጻናት ሚሊዮኖች
በአለም ዙሪያ ያሉ ሁሉ -
12:07 - 12:10ድምጻቸውን ከፍ አድርገው
-
12:10 - 12:13"ስፈልግ ነው የማገባው!"
ማለት መቻል አለባቸው! -
12:13 - 12:16(ጭብጨባ)
-
12:23 - 12:25አመሰግናለሁ!
(ጭብጨባ)
- Title:
- የህጻናት ያለእድሜ ጋብቻ ተከላካይ አርበኚት የትግል ጥሪ
- Speaker:
- ሜሞሪ ባንዳ
- Description:
-
ሜሞሪ ባንዳ የህይወት እጣዋ ከእህቶቿ የተለየ ሆነ እህቷ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወደ ባህላዊው ‹የስልጠና ካንፕ› ተላከች ሴት ህጻናትን ‹ወንድን በጾታ ግንኙነት እንዴት ማርካት እንደሚቻል› የሚሰለጥኑበት ካንፕ በዛም በ11 አመት ጨቅላ እድሜዋ ለእርግዝና ተዳረገች፡፡ ባንዳ ግን ባለመሄድ አቋሟ ጸናች ከዛ ይልቅ ሌሎችን በማደራጀት ለማህበረሰቡ መሪዎች የትኛዋም ሴት ህጻን 18 አመት ሳይሞላት በግዴታ መዳር እንደሌለባት በህግ ደረጃ እንዲጸድቅ ጥያቄ አቀረበች በዚህ አላቆመችም በአገር አቀፍ ደረጃ ትግሏን ገፋችበት.... ለመላው ማላውያን ሴት ህጻናት አመርቂ ውጤትም አስመዘገበች፡፡
- Video Language:
- English
- Team:
- closed TED
- Project:
- TEDTalks
- Duration:
- 12:38
Dimitra Papageorgiou approved Amharic subtitles for A warrior’s cry against child marriage | ||
Ahmed Omer edited Amharic subtitles for A warrior’s cry against child marriage | ||
Ahmed Omer accepted Amharic subtitles for A warrior’s cry against child marriage | ||
Ahmed Omer edited Amharic subtitles for A warrior’s cry against child marriage | ||
Ahmed Omer edited Amharic subtitles for A warrior’s cry against child marriage | ||
dagim zerihun edited Amharic subtitles for A warrior’s cry against child marriage | ||
dagim zerihun edited Amharic subtitles for A warrior’s cry against child marriage |