WEBVTT 00:00:01.014 --> 00:00:02.825 ዛሬ ንግግሬን 00:00:02.825 --> 00:00:04.891 ግጥም በማንበብ እጀምራለሁ 00:00:04.891 --> 00:00:08.026 ማላዊ ከምትገኝ ጓደኛዬ የተጻፈ ነው 00:00:08.026 --> 00:00:10.162 አይሊን ፒይሪ ትባላለች 00:00:10.162 --> 00:00:13.506 አይሊን ፒይሪ የ13 አመት ልጅ ነች 00:00:13.506 --> 00:00:19.380 ጽፈናቸው ከነበር የግጥም ስብስቦች መካከል ስፈልግ 00:00:19.380 --> 00:00:22.248 የሷን አስደናቂ ግጥም አገኘሁ 00:00:22.248 --> 00:00:24.245 በጣም ያነሳሳል! 00:00:24.245 --> 00:00:26.358 ስለዚህ እሱን አነብላቹሀለው 00:00:26.905 --> 00:00:30.503 ለግጥሙ የሰጠችው አርዕስ "ስፈልግ ነው የማገባው" ይላል 00:00:30.503 --> 00:00:33.359 (ሳቅ) 00:00:33.359 --> 00:00:35.890 ስፈልግ ነው የማገባው! 00:00:35.890 --> 00:00:40.790 እናቴ ልታስገድደኝ አትችልም እንዳገባ 00:00:40.790 --> 00:00:43.994 አባቴ ሊያስገድደኝ አይችልም እንዳገባ 00:00:45.526 --> 00:00:48.336 አጎት ፣ አክስቶቼ 00:00:48.336 --> 00:00:50.681 ወንድም ፣ እህቶቼ 00:00:50.681 --> 00:00:52.863 ሊያስገድዱኝ አይችሉም እንዳገባ 00:00:53.885 --> 00:00:56.254 ማንም በዚች አለም 00:00:56.254 --> 00:00:59.550 አይችልም ተገድጄ እንዳገባ 00:00:59.550 --> 00:01:02.499 ስፈልግ ነው የማገባው! 00:01:02.499 --> 00:01:05.077 ብትደበድቡኝም 00:01:05.077 --> 00:01:07.747 ብታባሩኝ እንኳን 00:01:07.747 --> 00:01:10.928 ምንም ብታደርጉ መጥፎ 00:01:10.928 --> 00:01:17.267 ስፈልግ ነው የማገባው! 00:01:17.267 --> 00:01:21.005 ሳልጨርስ አይደለም ሳልማር ትምህርቴን 00:01:21.005 --> 00:01:25.323 ሳይደረስ አይደለም ሳላድግ በእድሜ 00:01:25.323 --> 00:01:27.810 ስፈልግ ነው የማገባው! 00:01:28.831 --> 00:01:31.827 ይህ ግጥም ግር ሊላቹ ይችላል 00:01:31.827 --> 00:01:35.356 በ13 አመት ልጅ መጻፉ 00:01:35.356 --> 00:01:40.139 ግን እኔና አይሊን ከመጣንበት አካባቢ 00:01:40.139 --> 00:01:43.900 ይሄ ግጥም 00:01:43.900 --> 00:01:47.616 የአርበኞች ጥሪ ነው! 00:01:47.616 --> 00:01:50.541 እኔ ከማላዊ ነው የመጣሁት 00:01:51.191 --> 00:01:55.115 ማላዊ ደሀ ከሚባሉ አገራት አንዷነች 00:01:55.115 --> 00:01:57.994 በጣም ደሀ! 00:01:57.994 --> 00:02:02.522 የጾታ እኩልነት አጠራጣሪ የሆነባት አገር 00:02:02.522 --> 00:02:04.844 በዛች አገር በማደጌ 00:02:04.844 --> 00:02:08.095 በህይወቴ ውስጥ የራሴን ምርጫ ማድረግ አልችልም 00:02:08.095 --> 00:02:10.393 በህይወት የማንነት እድሎችን እንኳን... 00:02:10.393 --> 00:02:13.389 መመርመር አልችልም 00:02:13.389 --> 00:02:15.919 አንድ ታሪክ ልንገራችሁ 00:02:15.919 --> 00:02:18.381 ስለ ሁለት የተለያዩ ልጃገረዶች ነው 00:02:18.381 --> 00:02:22.026 ስለ ሁለት ውብ ልጃገረዶች 00:02:22.026 --> 00:02:24.580 እነዚህ ልጆች 00:02:24.580 --> 00:02:26.693 በአንድ ጣራ ስር አብረው ነው ያደጉት 00:02:26.693 --> 00:02:29.410 አንድ አይነት ምግብ እየበሉ 00:02:29.410 --> 00:02:32.173 አንዳንዴ አንድ ልብስ እየተጋሩ 00:02:32.173 --> 00:02:34.982 ጫማ አንኳን ሳይቀር 00:02:34.982 --> 00:02:39.649 ግን የህይወት ጉዟቸው የተለያየ ሆነ 00:02:39.649 --> 00:02:41.646 በሁለት የተለያዩ መንገዶች 00:02:43.039 --> 00:02:46.754 ሁለተኛዋ ልጅ ታናሽ እህቴ ናት 00:02:46.754 --> 00:02:51.677 ታናሽ እህቴ 11 አመት ይሆናት ነበር 00:02:51.677 --> 00:02:54.329 ባረገዘችበት ወቅት 00:02:56.029 --> 00:02:59.742 በጣም የሚያሳምም ነገር ነው! 00:03:01.352 --> 00:03:04.633 እሷ ብቻ አይደለችም እኔም ተጎድቻለሁ 00:03:04.633 --> 00:03:08.232 የጭንቅ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩት 00:03:08.232 --> 00:03:11.947 በባህላችን 00:03:11.947 --> 00:03:14.942 ለአቅመ ሄዋን በደረስን ጊዜ 00:03:14.942 --> 00:03:18.820 ወደ ልምምድ ካምፕ መሄድ ይኖርብናል 00:03:18.820 --> 00:03:21.118 በነዚህ ካምፖች 00:03:21.118 --> 00:03:24.973 ወንድን በጻታ ግንኙነት እንደምታስደስቱ ትማራላቹ 00:03:24.973 --> 00:03:26.761 ልዩ የሆነ ቀን አለ 00:03:26.761 --> 00:03:29.965 "በጣም ልዩ ቀን" ብለው የሚጠሩት 00:03:29.965 --> 00:03:32.519 በማህበረሰቡ የተቀጠረ ወንድ 00:03:32.519 --> 00:03:35.143 ወደ ካምፑ ይመጣና 00:03:35.143 --> 00:03:37.572 ከሴት ህጻናቱ ጋር እንዲተኛ ይደረጋል 00:03:39.252 --> 00:03:41.766 አስቡት እስቲ! እነዚህ ሴት ህጻናት ያለባቸውን ስቃይ 00:03:41.766 --> 00:03:44.516 በየቀኑ! 00:03:46.766 --> 00:03:49.925 አብዛኞቹ ልጃገረዶች ያረግዛሉ! 00:03:49.925 --> 00:03:52.542 በኤችአይቪ ኤድስ ይያዛሉ! 00:03:52.542 --> 00:03:54.882 ሌሎች በጾታ ግንኙነት የሚመጡ በሽታዎች ጭምር 00:03:55.692 --> 00:04:00.603 ትንሷ እህቴ እርግዝና ነበር የገጠማት 00:04:00.603 --> 00:04:04.666 አሁን 16 አመቷ ነው 00:04:04.666 --> 00:04:07.662 ሶስት ልጆች አሉዋት 00:04:07.662 --> 00:04:11.307 የመጀመሪያ ትዳሯ አልሰመረም 00:04:11.307 --> 00:04:14.604 ሁለተኛውም ቢሆን እንደዛው 00:04:14.604 --> 00:04:18.781 በሌላ በኩል ደግሞ ይህቺ ልጅ አለች 00:04:19.341 --> 00:04:21.314 የምታስደንቅ ናት! 00:04:21.314 --> 00:04:23.218 (ሳቅ) 00:04:23.218 --> 00:04:26.163 (ጭብጨባ) 00:04:27.723 --> 00:04:30.138 አስደናቂ ነች ያልኩት ስለሆነች ነው! 00:04:30.138 --> 00:04:33.203 በጣም አስደማሚ ናት! 00:04:33.203 --> 00:04:36.964 ያቺ ልጅ እኔ ነኝ! (ሳቅ) 00:04:36.964 --> 00:04:39.982 የ13 አመት ልጅ ሆኜ 00:04:39.982 --> 00:04:43.396 አድገሻል 00:04:43.396 --> 00:04:46.228 እድሜሽ ደርሷል 00:04:46.228 --> 00:04:49.595 ወደ ልምምድ ካምፑ መሄድ አለብሽ ሲሉኝ ነበር 00:04:49.595 --> 00:04:52.567 "ምን?" ነበር የኔ መልስ 00:04:52.567 --> 00:04:56.549 ወደ ልምምድ ካምፑ አልሄድም አልኩ 00:04:58.349 --> 00:05:01.112 አንድ ሴት ምን እንዳለችኝ ታውቃላቹ? 00:05:01.112 --> 00:05:04.734 ደደብ ልጅ ነሽ! ምንም የማይገባሽ! 00:05:04.734 --> 00:05:12.001 የማህበረሰባችንን፣ የእኛን ባህል አታከብሪም! 00:05:12.001 --> 00:05:15.809 እንቢ! ያልኩት የት እንደምሄድ ስለማውቅ ነው 00:05:15.809 --> 00:05:18.433 በህይወቴ ምን አንደምፈልግ ስለማውቅ ነው 00:05:19.773 --> 00:05:22.738 በልጅነት ብዙ ህልሞች ነበሩኝ 00:05:24.238 --> 00:05:27.883 በደንብ መማር እፈልግ ነበር 00:05:27.883 --> 00:05:30.363 ወደፊት ጥሩ ስራ አንዲኖረኝ 00:05:30.363 --> 00:05:32.122 እራሴን ጠበቃ ሆኜ እስለው ነበር 00:05:32.122 --> 00:05:34.832 ትልቅ ወንበር ላይ ተቀምጬ 00:05:34.832 --> 00:05:37.138 በሀሳብ የምስለው 00:05:37.138 --> 00:05:40.468 በየቀኑ በአእምሮዬ የሚመላለሰው እሱ ነበር 00:05:40.468 --> 00:05:42.302 ደግሞ አውቅ ነበር አንድ ቀን 00:05:42.302 --> 00:05:46.876 የሆነ ነገር፣ የሆነ ትንሽ ነገር ለ ማህበረሰቤ እንደማበረክት 00:05:46.876 --> 00:05:49.407 ግን እንቢ ካልኩኝ በኋላ በየቀኑ 00:05:49.407 --> 00:05:51.427 ሴቶቹ 00:05:51.427 --> 00:05:54.817 "እራስሽን ተመልከቺ እስቲ? ትልቅ ሆነሻል! እህትሽ አንኳን ልጅ አላት! 00:05:54.817 --> 00:05:56.303 አንቺስ?" ይሉኛል 00:05:56.303 --> 00:06:01.017 ይሄን ዘፈን ነበር በየቀኑ እሰማ የነበረው 00:06:01.017 --> 00:06:04.894 ይሄን ዘፈን ነበር በየቀኑ ልጆቹ ይሰሙ የነበረው 00:06:04.894 --> 00:06:09.043 ምንም ሳያደርጉ ሲቀሩ ማህበረሰቡ እንዲሆኑ የሚፈልገው እሱን ነው 00:06:11.524 --> 00:06:15.448 የኔንና የእህቴን ታሪክ ሳነጻጽረው 00:06:15.448 --> 00:06:20.185 ለራሴ "የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ?" አልኩ 00:06:20.185 --> 00:06:25.246 አንድ ነገር መለወጥ ለምንድ ነው የማልችለው? 00:06:25.246 --> 00:06:27.661 ያውም! ከጥንት ጀምሮ የነበረን ነገር 00:06:27.661 --> 00:06:30.169 በዛን ጊዜ ነው ሌሎቹን ልጆች የሰበሰብኳቸው 00:06:30.169 --> 00:06:32.723 ልክ እንደ እህቴ ልጆች ያላቸውን 00:06:32.723 --> 00:06:36.187 ይማሩ ነበር ግን ማንበብና መጻፍ ጠፍቶባቸዋል 00:06:36.187 --> 00:06:38.297 ኑና እርስ በራሳችን እንማማር አልኳቸው 00:06:38.297 --> 00:06:40.432 ማንበብና መጻፍ እንደገና እንሞክር 00:06:40.432 --> 00:06:44.240 ብእር እንዴት እንደሚያዝ፣ እንዴት እንደሚነበብ፣ መጽሀፍ እንደሚያዝ 00:06:44.240 --> 00:06:47.885 በጣም ትልቅ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው 00:06:47.885 --> 00:06:52.157 ስለ እነርሱ ትንሽ አወኩኝ 00:06:52.157 --> 00:06:55.594 የግል ታሪካቸውን ያጫውቱኝ ነበር 00:06:55.594 --> 00:06:57.405 በእናትነታቸው 00:06:57.405 --> 00:07:00.075 በየቀኑ ስለሚገጥማቸው ነገር 00:07:00.075 --> 00:07:02.072 ያኔ ሀሳብ መጣልኝ 00:07:02.072 --> 00:07:05.996 እነዚህ በኛ ላይ የሚሆኑትን ነገሮች ይዘን 00:07:05.996 --> 00:07:09.873 ለእናቶቻችን ለባህላዊ መሪዎቻችን ለምን አንነግራቸውም? 00:07:09.873 --> 00:07:11.870 እነዚህ ነገሮች ስህተት አንደሆኑ ለምን አናስረዳም? 00:07:11.870 --> 00:07:13.937 ለማድረግ የሚያስፈራ ነገር ነበር 00:07:13.937 --> 00:07:15.910 ምክንያቱም ባህላዊ መሪዎቻችን 00:07:15.910 --> 00:07:18.114 አምነው የተቀበሉት ልማድ ነው 00:07:18.114 --> 00:07:20.554 ለዘመናት የነበረ ነገር ነው 00:07:20.554 --> 00:07:22.481 ለመቀየር የሚከብድ ነገር 00:07:22.481 --> 00:07:25.105 ግን ለመሞከር ጥሩ የሆነ 00:07:25.105 --> 00:07:27.357 ስለዚህ ሞከርነው! 00:07:27.357 --> 00:07:29.865 በጣም ከባድ ነበር ግን ገፋንበት 00:07:30.245 --> 00:07:33.109 እናም አሁን በማህበረሰባችን 00:07:33.109 --> 00:07:35.669 የመጀመሪያዎቹ ሴቶች ነን 00:07:35.669 --> 00:07:39.036 መሪዎቻችንን ስንጫን 00:07:39.036 --> 00:07:43.425 እናም መሪዎቻችን ከጎናችን ቆሙው 00:07:43.425 --> 00:07:45.654 ማንም ሴት 18 አመት ሳይሞላት ማግባት የለባትም አሉ 00:07:45.654 --> 00:07:49.507 (ጭብጨባ) 00:07:53.502 --> 00:07:55.243 በማህበረሰባችን 00:07:55.243 --> 00:07:57.890 ለመጀመሪያ ጊዜ 00:07:57.890 --> 00:08:00.351 በህግ ደረጃ 00:08:00.351 --> 00:08:03.858 የመጀመሪያው ሴት ልጆችን የሚከላከል ህግ 00:08:03.858 --> 00:08:06.052 ሆነ! 00:08:06.052 --> 00:08:07.840 እዚህ ጋር አላቆምንም 00:08:07.840 --> 00:08:10.789 ወደፊት ተራመድን 00:08:10.789 --> 00:08:14.643 በኛ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለያንዳንዷ ሴት ህጻን መብት ለመዋጋት ቆረጥን 00:08:14.643 --> 00:08:17.429 በሌላም ማህበረሰብ ቢሆን 00:08:17.429 --> 00:08:21.562 የህጻናት የጋብቻ ህግ በቀረበበት ጊዜ 00:08:21.562 --> 00:08:25.208 በአገሪቱ ፓርላማ ተገኝተን ነበር 00:08:25.208 --> 00:08:29.294 በየቀኑ የፓርላማ አባላቱ በሚገቡበት ሰአት 00:08:29.294 --> 00:08:32.383 እባካችሁ ህጉን ደግፉ! እንላቸው ነበር 00:08:32.383 --> 00:08:37.142 እዚህ አንዳለው አይነት ቴክኖሎጂ አልነበረንም 00:08:37.142 --> 00:08:39.139 ግን ትናንሽ ስልኮች ነበሩን 00:08:39.139 --> 00:08:44.169 ስለዚህ ቁጥራቸውን ፈልገን ለምን በጽሁፍ መልክት አንልክላቸውም? ተባባልን 00:08:44.178 --> 00:08:47.428 አደረግነው! ጥሩ ነገር ነበር! 00:08:47.428 --> 00:08:49.448 (ጭብጨባ) 00:08:49.448 --> 00:08:52.421 ህጉ ከጸደቀ በኋላ መልሰን በጽሁፍ መልክት ላክንላቸው 00:08:52.421 --> 00:08:54.849 "ህጉን ስለደገፋቹ እናመሰግናለን" 00:08:54.849 --> 00:08:55.919 (ሳቅ) 00:08:55.919 --> 00:08:59.264 ፕሬዝዳንቱ ህጉን በፊርማው ሲያጸድቅ 00:08:59.264 --> 00:09:02.630 ቋሚ ሆነ! ይሄ ተጨማሪ ድል ነበር 00:09:02.630 --> 00:09:08.482 አሁን በማላዊ የጋብቻ እድሜ 18 አመት ነው ከ15 እስከ 18 00:09:08.482 --> 00:09:12.127 (ጭብጨባ) 00:09:14.495 --> 00:09:18.071 የህጉ መጽደቅ በራሱ ጥሩ ነገር ነበር 00:09:18.071 --> 00:09:21.113 ግን አንድ ነገር ልንገራቹ 00:09:21.113 --> 00:09:25.501 18 አመት የጋብቻ እድሜ የሆነባቸው አገሮች አሉ 00:09:25.501 --> 00:09:29.773 ግን በየቀኑ የሴቶች የህጻናት ለቅሶ እየሰማን አይደለም? 00:09:29.773 --> 00:09:35.416 በየቀኑ የሴት ህጻናቱ ህይወት ይባክናል 00:09:35.416 --> 00:09:41.870 ከመሪዎቻችን አሁን የሚያስፈልገው የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ነው 00:09:41.870 --> 00:09:44.239 ቃል ማክበር ማለት 00:09:44.239 --> 00:09:49.951 የሴት ህጻናትን ጉዳይ ሁሌም ከልብ መያዝ ነው 00:09:49.951 --> 00:09:53.712 እንደ ሁለተኛ ደረጃ መታየት የለብንም 00:09:53.712 --> 00:09:57.950 ማወቅ ያለባቸው ነገር! ሴቶች በዚህ ክፍል ውስጥ እንዳለነው 00:09:57.950 --> 00:10:01.000 ሴት ብቻ! ልጆች ብቻ! አይደለንም! 00:10:01.000 --> 00:10:02.980 ከምንም ነገር በላይ ነን! 00:10:02.980 --> 00:10:04.893 የተሻለ ማድረግ እንችላለን 00:10:04.893 --> 00:10:07.888 ስለ ማላዊ ሌላው ነገር 00:10:07.888 --> 00:10:10.790 በማላዊ ብቻ አይደለም በሌሎችም አገሮች 00:10:10.790 --> 00:10:14.575 ያሉት ህጎች 00:10:14.575 --> 00:10:20.426 ህግ እስካልተፈጸመ ድረስ ህግ አይሆንም 00:10:20.426 --> 00:10:23.839 በቅርብ ያጸደቅነው ህግ 00:10:23.839 --> 00:10:26.463 በሌሎች አገራትም ያለው ህግ 00:10:26.463 --> 00:10:30.387 በየአካባቢው መሰራጨት አለበት 00:10:30.387 --> 00:10:32.570 በየማህበረሰቡ 00:10:32.570 --> 00:10:37.956 የሴት ህጻናት ጉዳይ አስቸጋሪ በሆነበት ሁሉ 00:10:37.956 --> 00:10:42.716 በየቀኑ በማህበረሰብ ደረጃ ሴት ህጻናት ከባድ ችግር ይጋረጥባቸዋል 00:10:43.274 --> 00:10:48.359 ስለዚህ እነዚህ ሴት ህጻነት የሚጠብቃቸው ህግ አንዳለ ካወቁ 00:10:48.359 --> 00:10:51.145 ተነስተው እራሳቸውን መከላከል ይችላሉ 00:10:51.145 --> 00:10:54.816 ምክንቱም የሚጠብቃቸው ህግ እንዳለ ስለሚያውቁ ነው 00:10:57.254 --> 00:11:01.363 ሌላ ማለት የምፈልገው 00:11:01.363 --> 00:11:05.961 የሴት ህጻናት፣ የሴቶች የትግል ድምጽ 00:11:05.961 --> 00:11:08.724 ውብ ነው! ሁሉም ጋር አለ 00:11:08.724 --> 00:11:11.905 ይሄንን ግን ብቻችንን ማድረግ አንችልም 00:11:11.905 --> 00:11:14.575 ወንዶች ትግላችንን ሊቀላቀሉን 00:11:14.575 --> 00:11:16.525 ከጎን ሆነው አብረን መስራት አለብን 00:11:16.525 --> 00:11:19.103 የጋራ ሀላፊነት ነው! 00:11:19.103 --> 00:11:21.843 ለሴት ህጻናት የሚያስፈልገውን ሁሉ መሟላት አለበት 00:11:21.843 --> 00:11:27.601 ጥሩ ትምህርት፣ ከሁሉም በላይ በ11 አመት አለመዳር 00:11:30.085 --> 00:11:32.953 በተጨማሪ 00:11:32.953 --> 00:11:36.018 አንድ ላይ ከሆንን 00:11:36.018 --> 00:11:39.966 ህግን 00:11:39.966 --> 00:11:43.135 ባህላዊና ፖለቲካዊ ዳራን 00:11:43.135 --> 00:11:47.906 የሴት ህጻናትን መብት የሚነፍገውን መቀየር እንችላለን 00:11:47.906 --> 00:11:52.964 እዚህ ከፊታቹ በመሆን ዛሬ 00:11:52.964 --> 00:12:00.004 ለትውልዶች ያለ እድሜ ጋብቻን ማስቆም እንደምንችል እነግራቹሀለው 00:12:00.677 --> 00:12:02.860 በዚች ቅጽበት! 00:12:02.860 --> 00:12:07.294 ሴት ህጻናት ሚሊዮኖች በአለም ዙሪያ ያሉ ሁሉ 00:12:07.294 --> 00:12:09.895 ድምጻቸውን ከፍ አድርገው 00:12:09.895 --> 00:12:13.099 "ስፈልግ ነው የማገባው!" ማለት መቻል አለባቸው! 00:12:13.099 --> 00:12:16.144 (ጭብጨባ) 00:12:23.284 --> 00:12:25.219 አመሰግናለሁ! (ጭብጨባ)